No Touching
Date posted: Tuesday, March 24, 2020
የእኛ ሀገር የኑሮ ሁኔታ ማህበራዊ ርቀትን በቶሎ ለመተግበር አስቸጋሪ ቢሆንም የቫይረሱ ስርጭት ከሚያደርሰው የከፋ ጉዳት ለመትረፍ ግን የጤና ባለሞያዎችን ምክር መስማት ግዴታ ነው። መንግስትም በቻለው አቅም ጊዜው #ሳይረፍድ የተሻሉ አማራጮችን ቢፈልግ መልካም ነው። ፎቶው አሁን መገናኛ አካባቢ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።
እኛ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ካላዳመጥን፣ የምንባለውን ካልተገበርን ፣ ቸልተኝነታችን ነገ ሳይሆን አሁን ካልተገታ ፣ አታድርጉ የምንባለውን ከማድረግ ካልተቆጠብን ፣ በምን አይነት መልኩ ነው ይህን ቫይረስ ምንቋቋመው ?
የግድ ለመጠንቀቅ ብዙ ሺ ሰው መታመም አለበት ? ሌሎች ያዩትን መከራ ማየት አለብን? ለመጠንቀቅ ሰው መሞት አለበት? ኮሮና ቫይረስ ቀልድ አይደልም! የምንባለውን ካላዳመጥን ፤ የሚባለውን ካልተገበርን ጣልያን እየሆነች እንዳለው መሆናችን አይቀርም።
እጅግ በጣም ቀላል የሆኑ የቫይረሱን የመከላከያ መንገዶችን በመዘናጋት ፣ በፌዝ ፣ በቀልድ እያየን የማንወጣው አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ አደራ። አትፍሩ ማለት አትጠንቀቁ ማለት አይደለም! በሲያንስ ለሌሎች ወገኖች እናስብ !
ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
FOLLOW US ON
X